ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በባለፉት ሦስት ወራት ከ301 ሚሊዮን ብር በላይ ለደንበኞቹ የብድር አገልግሎት መሰጠት መቻሉን ገለጸ

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የ2018 የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት የግምገማ መድረክ በዛሬው እለት አካሂዷል

በግምገማ መድረኩም የቅርንጫፎችና የዋናው መሥሪያ ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በመድረኩም በተቋሙ በባለፉት ሦስት ወራት በብድር ስርጭት ረገድ 324 ሚሊዮን ብር ብድር ለማሰራጨት ታቅዶ 301 ሚሊዮን ብር ለደንበኞቹ የብድር አገልግሎት መስጠት የተቻለ ሲሆን ይህም የእቅድን 94% ማሳካት መቻሉን የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተሾመ አበበ ገልጸዋል።

የቁጠባ አሰባሰብን በሚመለከት 517 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 501 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን በውዝፍ አሰባሰብም የእቅድን 97% በማስመለስ ውጤታማ አፈፃፀም ማስመዝገብ መቻሉን ኃላፊው አብራርተወዋል።

የሴቶችንና ወጣቶችን በብድርና ቁጠባ አገልግሎት ተጠቃሚነት ከማሳደግ አንፃር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን የገለጽት ኃላፊው በሩብ ዓመቱ በዋስትና ፈንድ 47 ሚሊዮን ብር ለኢንተርፕራይዞች ብድር ስርጭት መከናዋኑን ገልጸዋል።

ተቋሙ ተደራሽነት በማሳደግ የላቀ የደንበኞች አገልግሎት በመሥጠትና ዕርካታ በማሳደግ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ውጤታማነትን በማስቀጠል በኩል በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ ኃላፊው አመላክተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *