ከፌደራል እና ከክልል የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በአስተዳደሩ የተፈጠሩ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንድስትሪዎችን ጎበኙ

በጉብኝታቸውም በድሬዳዋ አስተዳደር የተፈጠሩ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የኢኮኖሚ አቅም በማሳደግ ሰፊ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ተመልክተናል ብለዋል።

አስተዳደሩ ለአምራች ኢንደስትሪ ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት በተግባር በውጤት የተደገፈ ተጨባጭ ስራ አይተናል ሲሉም ገልጸዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የንግድ ኢንድስትሪና ኢንቨስትመንት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲ ሙክታር በወቅቱ እንዳአሉት በባለፉት ጊዚያት ቢሮው ከPETCO Ethiopia ጋር በመተባበር ወጣቶችን እና ሴቶችን በኢንዱስትሪው ዘርፍ በኢንተርፕራይዝ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻል አንጻር ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

ለዜጎች የስራ እድል እንዲፈጠር የውጭ ምርት የማስገባት ፍላጎትን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እና ኤክስፖርትን ከፍ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውንም አስረድተዋል።

በአስተዳደሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውንም አንስተዋል።

ኢንዲስትሪዎቹ ተወዳዳሪነታቸው ከፍ እንዲል በቴክኖሎጂ ሽግግር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አቶ አብዲ ገልጸዋል።

ከተጎበኙት አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችም መካከል ሀስ የህክምና መሳሪያ ማምረቻ፣ የድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅት፣ድቄት ማምረቻዎች፣የወተት ማቀነባበሪያ፣ የብረታብረት ማቅለጫ፣ጨርቃጨርቅ ማምረቻ፣ፕላስቲክ ሪሳይክል ማምረቻ፣ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ሌሎችም ይገኙበታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *