የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የከተሞች መስፋፋትና በከተሞች እድገት ላይ ከሚሰሩ ባለድርሻ ጋር ውይይት አድርጓል።
የውይይት መድረኩ በዋናነት የከተማዋን ፈጣን እድገት ታሳቢ ያደረገ የከተማ ማስፋፊያ በዘመናዊ ፕላን ለመመራት በሚያስችል ጉዳዮች ላይ የሚመክር መድረክ መሆኑ ተገልጿል።
በመድረኩም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኢማጅ አብደላ በወቅቱ እንዳሉት ከተማነት በፈጣን እድገት እየተስፋፋ መምጣቱን አውስተው ቢሮው ያንን እሚመጥን ዘመናዊ የከተማ ፕላን ለማዘጋጀት የሚያስችል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ከተሞች እንዴት፣ መቼ፣ ለምንና በምን መመራት እንዳለባቸው የሚያሳይ ግልጽ አሰራር ሊኖራቸው እንደሚገባም ጠቁመዋል።
በዚህም ከተማዋን በፖሊሲና በፕላን ለመምራት እንዲያስችል የዘርፉ ተቋማት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።
በመድረኩም ከከተማዋ ፈጣን እድገት መስፋፋት ጋር በተያያዘ ለቀጣይ 30 ዓመት የከተማዋ ፕላን ምን መምሰል እንዳለበት የሚያሳይ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።


