በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በእውቀትና በክህሎት የሚመራ ዘመናዊ አሰራርን የተከተለ ቅንጅታዊ ስራ መኖር እንዳለበት ተገለፀ

2018 ዓም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ቴክኒካል ኮሚቴ አባላት የውይይትና አቅም ልማት መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ምክትል ሃላፊና እና አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ አብዲ ሙክታር እንደ አገር የኢንዱስትሪው ዘርፍ እንዲስፋፋና ለሀገሪቱ አጠቃላይ እድገት ተገቢው ሚና እንዲኖረው ማድረግ ብሎም የውጪ ንግድን እንዲያድግ እንዲሁም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ማስቀረት ላይ ትኩረት እንዲሰጥ ማድረግ ”የኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ አላማዎች ተጠቃሽ ጉዳዮች መሆናቸውን ሃላፊው ጠቁመዋል።

በአስተዳደሩ እንደ ሀገር ከተቀመጠው ኢቲዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መረሀ ግብር በተናበበ መልኩ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ አራት አመታት መዝለቁን ጠቅሰው በንቅናቄው የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ከጊዜ ወደ ጊዜ አንፃራዊ ለውጥ እያመጡ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

እንደ አስተዳደር በንቅናቄው አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች እንዲከፈቱና ነባር ኢንዱስትሪዎችን ከመደገፍ ረገድም የተቀናጀ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ በዚህም ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አንፃር ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አቶ አብዲ ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ በንቅናቄው የበለጠ ውጤት ከማስመዝገብ አኳያ የድጋፍ እና ክትትል ክላሰተር ኮሚቴ አባላት በሙሉ አቅም ከመንቀሳቀስ አንፃር ክፍተት እንዳለ ይህንንም ለመቅረፍ በቀጣይ በጋራ እቅድ የተመራ ተግባር ማከናወን እንደሚገባ ሐላፊው ጨምረው ገልፀዋል።

በወቅቱ በተደረገ ውይይት የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ማጠናከር ምርት ልማትና ተወዳዳሪነትንና አስተዋዕዖ ለማላቅ ፣ የሰው ኃይል ልማት ላይ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት በኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ መስራት እንደሚገባ በጉልህ ተነስቷል።

በመድረኩ የአቅም ግንባታና ምርምር ተቋማት ፣ የመሰረተ ልማት ፣የፋይናንስና ጉሙሩክ ጉዳዮች፣የግንባታና ግብይት፣የኢንቨስትመንትና የግል ዘርፍ የንቅናቄ አባላት መካከል በቀጣይ በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ የፊርማ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *