ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ከድሬዳዋ ሳይንስ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በኤስ. ቲ. አይ ፖሊሲ ፣ የስታርታፕ አዋጅ እና ፈንድ ማፈላለግና ማስተዳደር ላይ የግንዛቤ ማዳበሪያ ስልጠና ሰቷል።
ኢንጂነር መሃዲ መሃመድ ሳይንስ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ሃላፊ ተክኖሎጂና አይሲቲን ማጎልበትና መጠቀም ዘመኑ የሚጠይቅ አለም የሚመራበት ሁኔታ መሆኑን ገልፀው እንደ አገርም ሆነ እንደ ድሬደዋ በተለያዩ መስኮች ቴከኖጂን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት በሰፊው መከናወን ጀምረዋል ብለዋል።
ዘርፉን በፖሊሲና ስትራቴጂ ለመደገፍ በተለይ አሁን አዲስ የተሻሻለ አዋጅ በማፅደቅና ወደ ተግባር ማስገባት መቻሉን የተካሄደው የግናዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በዘርፉ ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች አቅምን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።
በቀጣይም በተለያዩ ደረጃዎች መሰል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ለማወቅ ተችሏል።


