በስልጠናው መድረክ ላይ ንግግር ያደርጉት የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሚልኬሳ ሙሜ ሀገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን የአባላትና የፈፃሚዎችን አቅም መገንባት ላይ ፓርቲው ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልፀው ይህ የግንዛቤ ማዳበሪያ ስልጠናም አባላትን በክህሎት ፣ በዕውቀት፣ እንዲሁም በተግባር አፈፃፀም ከማብቃት አኳያ የጐላ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የመረጃ ማፍራት እና ማብቃት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አቤል ሞላ በበኩላቸው ስልጠናው የህብረቱ አባላት የፓርቲውን ፕሮግራም ለማስፈፀም በአንድ አካል ሊከውኗቸው በሚችሉ የተልዕኮ መመሪያዎች ላይ በጥልቀት ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል።


