በመፍጠርና በመፍጠን እሳቤ የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄዎችን ለመመለስ በ9 ወር ውስጥ 1287 ቤቶች መገንባቱ ተገለፀ።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የጀርመን ሳይት የቤት ልማት ከሚከናወንባቸው ሳይቶች ውስጥ አንዱ ነው።
የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በመዲናዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን በጎበኙበት ወቅት፤ የጀርመን ሳይት የቤት ልማት ፕሮጀክትን ተመልክተዋል።
የጀርመን ሳይት ሕንፃዎች ባለ 15 ወለል ሲሆኑ ፤ እያንዳንዱ ህንፃ 52 መኪና ማቆም የሚችል ፓርኪንግ እንዳለው ተመላክቷል።
ሕንፃዎቹ የስፖርት ማዘውተሪያዎች እና የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ያሏቸው በመሆኑ ዘመናዊ አኗኗርን ለዜጎች የሚያላብሱ መሆናቸው ተገልጿል።


