በድሬዳዋ አስተዳደር 36ኛው አለም አቀፍ የሕጻናት ቀን “የሕጻናት ጥበቃና የመጫወት መብት ለሁለም ሕጻናት “በሚል መሪ ቃል በወረዳ 03 በኮሪደር ስፍራ ላይ በተለያዮ መርሃ ግብሮች በድምቀት ተከብሯል።

በመርሃ ግብሩም የወረዳው ሰራ አስፈጻሚ አቶ ምትኩ ሁነኘው ተገኝተው እንደገለጹት ህጻናት ጥበቃ ሊደረግላቸው እና የመጫወት መብት ሲሰጣቸው የአእምሮ የአካል እድገታቸዉ ይጨምራል ከማሕበረሰቡ ጋር በቀላሉ ይግባባሉ ፣ሐሳባቸዉን በነጻነት ይገልጻሉ ስለዚህም የሕጻናት መብት እና ተሳትፎ እንዲጠበቅና እንዲያድግ ሁሉም የበኩሉን አስተዎፆ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

ሕጻናት የመጫዎት መብታቸው እንዳይነፈግ ሁሉም ማሕበረሰብ ጥበቃ እንዲያደርግላቸው ግንዛቤ መፍጠር ይገባል በማለት ለህጻናቱ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመርሃ ግብሩም ላይ ከተለያዩ ትምህርት ቤት የተውጣጡ ተማሪዎች የጥያቄ እና መልስ ውድድር እንዲሁም የተለያዮ አዝናኘ ጫዎታዎችን አካሂደዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *