በሀገረ ፈረንሳይ ከሚገኝ ካስክ ኤፒፒዩአይ ከተሰኘ ድርጅት የመጣው የከፍተኛ ባለሞያዎች ልዑክ ለድሬዳዋ ፖሊስ ድንገተኛ የእሳት አደጋ መከላከል እና መቆጣጠር ዲቪዥን፣ ለድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ባለሞያዎች እንዲሁም ከሀረሪ አና ከሶማሌ አጎራባች ክልል ለመጡ ለድንገተኛ እሳት አደጋ መከላከል እና መቆጣጠር ሰራተኞች ድንገተኛ እሳት አደጋ መከላከል እና መቆጣጠር ላይ እየሰጠ የሚገኘው ስልጠና ቀጥሏል፤ በዛሬው ዕለት ስልጠናው በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ጊቢ ውስጥ ተሰቷል።
በዚህም የድሬዳዋ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ መከላከል እና መቆጣጠር ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ፈጠነ ካሳዬ በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ጊቢ ውስጥ ለስልጠና የሚጠቅሙ በርካታ ቁሳቁሶች በመኖራቸውን ተናግረው፤ ይህም ሁሉም ሰልጣኝ በቀላሉ ስልጠናውን በተግባር እየተለማመደ አስፈላጊውን ዕውቀት ጨብጦ ብቁ እንዲሆን እንደሚያስችለው አመላክተዋል።
ኢንስፔክተር ፈጠነ አያይዘውም ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙ ባለሞያዎች በዘርፉ የረጅም ዓመታትን ልምድ እና እውቀት ያካበቱ በመሆኑ በርካታ ተሞክሮዎችን ማግኘታቸውን ጠቅሰው፤ በአንፑላንሶች ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ በምን መልኩ እንደሚሰጥ መሰልጠናቸውንም አብራርተዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከፅንሰ ሃሳብ በዘለለ ስልጠናውን በተግባር ተኮር እየሰለጠንን መሆኑ አዳዲስ እውቀት እንድንገበይ አስችሎናል ሲሉ ተናግረዋል።


