ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ እና ስዊፍት ትራንስፖርት በኤሌትሪክ ትራንስፖርት ዘርፍ ተሰማርተው መስራት የሚፈልጉ የድሬዳዋ ወጣቶችን ለማገዝ በጋራ እንደሚሰሩ አስታወቁ

በዛሬው ዕለት ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ እና ስዊፍት ትራንስፖርት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተሾመ አበበ ስምምነቱ የፋይናንስ እጥረት ያለባቸው እና በትራንስፖርቱ ዘርፍ ተሰማርው መስራት የሚፈልጉ የድሬዳዋ ወጣቶች በድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በመቆጠብ የብድር ምችችት በማድረግ የመኪና ባለቤት እንደሚሆኑ የሚያደርግ ስምምነት እንደሆነም ገልፀወዋል ።

ከዚህ ቀደም ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ከሌሎች ከባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ጋር በጋራ ሲሰራ እንደነበር የተቋሙ ኃላፊ አቶ ተሾመ ገልፀው፤ አሁን ላይ ከባለ አራት እግር የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ጋር በጋራ የሚሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የስዊፍት ትራንስፖርት ስራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ አሸብር በበኩላቸው በድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በኩል የፋይናንስ አቅርቦት እና ምችችት ተከናውኖ በስዊፍት ትራንስፖርት በኩል የሚመጡ ተሽከርካሪዎችን ለከተማው ወጣቶች እንዲሁም በአጠቃላይ በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ሁሉ የማድረስ ስራ እንደሚሰራና ይህም ወጣቶች በከፍኛ ደረጃ ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ብሩክ አያይዘውም ስምምነቱ በዋናነት ለድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ወጣቶች በኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የሚረዳ መሆኑን አመላክተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *