20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በአስተዳደሩ በተለያዮ መርሃ ግብሮች በድምቀት ይከበራል”

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን

በዓሉ “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚከበር ተገልጿል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን በዛሬው እለት ለሚዲያ አካላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት የዘንድሮ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ሲከበር ሀገራችን በብዙ ስኬቶች ውስጥ ሆና የምታከብረው መሆኑ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው መሆኑን ገልጸዋል።

በባለፉት አመታት በህዝብ ድጋፍ የአንድነታችን እና የብሔር ብሔረሰብ አርማ የሆነው የህዳሴ ግድብ የተጠናቀቀበት እና የኢትዮጵያ ማንሰራራት የጀመረበት ስኬታማ ዓመት መሆኑን ተናግረዋል።

በዘንድሮ ዓመትም የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማሳያ የሆነው ፍትሃዊ ሀገራዊ ምርጫ የሚካሄድ መሆኑእና ለዚህም በቂ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።

በአስተዳደሩ የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀንም ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ዜጎች ማንነታቸውን እና ባሕላቸውን የሚያሳዩበት ትልቅ በዓል መሆኑንም ተናግረዋል።

20ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል በድምቀት እና በልዩ ሁኔታ ለማክበርም በቂ ዝግጅት መደረጉን አንስተው በዓሉ በአስተዳደር ደረጃ በሲሞፖዚየም በቶክ ሾ ው እና በተለያዩ ዝግጅቶች በሴክተር እና በወረዳዎች በድምቀት እንደሚከበር ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን አስታውቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *