በደቡብ አፍሪካ በተዘጋጀው የቡድን 20 (G-20) አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያ ጥቅም የሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ ውይይት መደረጉን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ገለፁ።
ከግሎባል ፈንድ ተጠቃሚ አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ፈንዱ በቀጣይ ዓመት የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ልገሳ እንዲደረግ ኢትዮጵያ ሰፊ ጥረት ማድረጓን ነው የገለፁት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጋር ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውንም ጠቅሰው፤ በኢትዮጵያ እያታየ ያለው የከተማ ለውጥ እና ትልቅ ፕሮጀክቶች መጠናቀቅ መደነቃቸውንም አንስተዋል።
የቡድን ሃያ (G-20) ጉባኤ በአፍሪካ ምድር ሲካሄድ የመጀመሪያው እንደመሆኑ በጉባዔው የአፍሪካ ጉዳይ በስፋት መነሳቱንም ተናግረዋል።
ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ መሪዎች ጋር በነበረ ውይይት የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን መነሳቱን ሚንስትሩ ተናግረዋል።
ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ጋር በተደረገ ውይይት ኢትዮጵያ በጀመረቻቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች መደነቃቸውን ጠቅሰው የቢሾፍቱ ኤርፖርትን በሚመለከትም ስኬታማ ውይይት መደረጉን ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል።


