የኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ የድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ እና የኮሪደር ልማት ግንባታን ጎበኙ

#DGC ህዳር 15/2018

የኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ በድሬዳዋ አስተዳደር ተገንብቶ በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት እየሰጠ ያለው ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ እና የኮሪደር ልማቶችን ጎብኝተዋል ።

ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሙስናን ለመከላከልና ብልሹ አሰራሮችን ቀድሞ ከመቆጣጠር አንፃር በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ የሚከወንና የስራ ባህልን የሚቀይር በመሆኑ በድሬዳዋ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ የኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ተናግረዋል ።

የኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ በድሬዳዋ አስተዳደር ባደረጉት ጉብኝት በአስተዳደሩ በቅርቡ ተቋቁሞ ሥራ የጀመረው ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከልንና በነምበርዋን እና በከዚራ አካባቢ የተሰሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል ።

ዶ/ር መኩሪያ በሰጡት አስተያየት ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሙስናን ለመከላከልና ብልሹ አሰራሮችን ቀድሞ ከመቆጣጠር አንፃር በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ የሚከወንና የስራ ባህልን የሚቀይር በመሆኑ በድሬዳዋ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም በኮሪደር ልማት ሥራዎች ረገድም በአስተዳደሩ የተያዘው ሥራ የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው የከተማዋን ውበትና ለነዋሪዎች ምቹ ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም ጠቁመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *