በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር የሆኑት ክቡር አሌክሲስ ላሜክ፥ ወደ ‘ትንሿ ኢትዮጵያ’ ድሬ በመምጣታቸው ከልብ ደስ ብሎኛል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም፥ በኢትዮጵያ ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ለፕሬዝዳንት ማክሮን ያቀረቡትን ግብዣ ተከትሎ የተደረገው ይህ የሥራ ጉብኝት፥ ታሪካዊውን የድሬዳዋ እና የፈረንሳይ ግንኙነት በይበልጥ የሚያጠናክር ነው።

16 የኢንቨስትመንት ቡድን አባላትን ከያዘውና በአምባሳደር ላሜክ ከተመራው ልዑክ ጋር በነበረን ቆይታ የእህትትማማች ከተሞችን ግንኙነት ለማሳደግ፥ በባህል እና ቱሪዝም መስኮች ድጋፍ ለማድረግ፥ እንዲሁም የፈረንሳይ ባለሀብቶች በአስተዳደራችን በሚገኙ የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ተሰማርተው ማልማት በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ምክክር አድርገናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *