ልዑኩ ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ጋር እንዲሁም ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በማህበራዊ ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በዲፕሎማሲው መስክ ስራዎችን በተጠናከረ መልኩ መስራት በሚቻልባቸው ነጥቦች ላይ ምክክር የሚያደርግ ይሆናል።
ልዑኩ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ በክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ በክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊ፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።


