“የመደመር መንግስት እይታ፤ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ በ3ኛ ዙር ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የብልፅግና ፓርቲ አባላት የመንግስት ሰራተኞች ስልጠና ተጠናቀቀ

“የመደመር መንግስት እይታ፤ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ በሁለት ዙር የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና መጠናቀቁን ተከትሎ በ3ኛ ዙር ከህዳር 26-27/2018 ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የሁሉም የብልፅግና ፓርቲ አባላት የመንግስት ሰራተኞች ስልጠና ተጠናቋል።

በሁለቱ ቀናት ቆይታ “የመደመር መንግስት እይታ ፣ የግብርና እና የገጠር ልማት ትራንስፎርሜሽን እምርታ፣ የኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን እምርታ፣ የከተማ ልማት እና የቱሪዝም እምርታ” በሚሉ ርዕሶች የስልጠና የተሰጠ ሲሆን የስልጠናው ዋንኛ አላማም የመደመር መንግስት የሀገርን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በተለዩ ዋናዋና ዘርፎች ያስቀመጣቸውን የልማት ትልሞችንና የትግበራ አቅጣጫዎችን በተመለከተ የብልፅግና ፓርቲ አባል የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ጥልቅ የሆነ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና እንደየ ስራ ባህሪያቸው የተቀመጡ አቅጣጫዎች ሳይንጠባጠቡ በፈጠራ፣ ፍጥነት እና ዝላይ በታከለበት አካሄድ እንዲተገበሩና የሚፈለገው ሁለንተናዊ ብልፅግና የተረጋገጠባትን ታላቅ ሀገር በመፍጠር ሂደት ውስጥ የተጣለባቸውን ድርብ ኃላፊነት በሚገባ በመወጣት አሻጋሪ ትውልድ መሆናቸው በተግባር እንዲያረጋግጡ ለማስቻል መሆኑን በስልጠናው ማጠቃለያ ተመላክቷል።

በተሰጡ የስልጠና ርዕሶች ዙሪያ ሰልጣኞች ሰፊ ጊዜ ወስደው የተወያዩ ሲሆን በማጠቃለያው ላነሷቸው የተለያዩ ጥያቄዎችም ስልጠናውን የሰጡት አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀት ከመደበኛ ስራቸው ጋር በማስተሳሰር በከፍተኛ ትጋት ተግባራዊ በማድረግ እንደ አስተዳደር ብሎም እንደሀገር በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ለውጦችን እውን በማድረግ ረገድ የሚጠበቅታቸውን ሁሉ በሚገባ እንዲወጡም የቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም መድረኩ የሀገራችንን ሁለንተናዊ እድገት የተረዳንበት እና በቀጣይ ሀገራዊ አቅጣጫዎች የራሳችንን አሻራ ለማሳረፍ እንድንጥር የሚያግዘን ነው ብለዋል።

በሁለቱ ቀን መድረክም ከድሬደዋ ጤና ቢሮ ጋር በመቀናጀት ለሰራተኛው የነፃ ጤና ምርመራ አገልግሎት በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *