” በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ ቃል ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የብልፅግና ፓርቲ አባላት መምህራን ፣ ተማሪዎች እና የአስተዳደር ሠራተኞች የሚሰጠው ስልጠና ለሁለት ቀን የሚቆይ ነው፡፡
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም የዛሬው ስልጠና አላማ መላው አመራር እና አባላቱ የግብርና ትራንስፎርሜሽን እና የገጠር ትራንስፎርሜሽን እንዲሁም በኢንደስትሪ ልማት ምንነት አስምልክቶ ግንዛቤ እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡
በግብርናና ኢንደስሪው ላይ የታየው እምርታ ትኩረት ያደረገ ሰነድ በዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት ተደርጎ ከተሳታፊዎችም የተለያዩ ሃሳብና አስተያየቶች ተሰጥተውበት የመጀመሪያው ቀን የስልጠና መርሀግብር ተጠናቋል፡፡


