በኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተፃፈው በመደመር ትውልድ መፅሀፍ ሽያጭ እንዲሁም በአስተዳደሩ ድጋፍ ዘመናዊ እና ደረጃውን የጠበቀ የእመርታ ቤተ-መፅሀፍ ተገንብቷል ። በዛሬው እለትም ለቤተ-መጽሀፍቱ የሚሆኑ ግብአቶች ርክክብ ፕሮግራምም ተካሂዷል ።
በመርሀ-ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር የእምርታ ቤተ-መፅሀፍትን ከመፅሀፍት ግብአት አንስቶ በቴክኖሎጂም መደገፍ እንደሚገባ ተናግረው ለእምርታ ቤተ-መጽሀፍት የሚውሉ የተለያዩ መፅህፍቶችን ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት እና ግለሰቦችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
በዛሬው እለትም ለእምርታ ቤተ-መፅሀፍት ከድሬዳዋ ፣ ከሀረማያ ዩኒቨርስቲ እና ከአዲስ አበባ የመጡ የተለያዩ መፅሀፍቶች መረከባቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ባህል እና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወንደሰን አባይ ተናግረው እስካሁን ድረስም ከ 32 ሺህ በላይ መፅሀፎች ድጋፍ እንደተደረጉና በቀጣይም መሰል ግብአቶችን የማሰባሰቡ ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው አቶ ወንደሰን ያስታወቁት ።


