ስልጠናው በዋነኝነት በግብርናው፣ በማኑፋክቸሪንግ ፣ በቱሪዝም እንዲሁም በከተማ ልማት ዘርፎች “በመደመር መንግስት ዕይታ ፤ የዘርፎች ዕመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ በብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት የመንግስት ሰራተኛ እና የፓርቲ አባላት እንዲሁም ነዋሪዎች በዘርፎቹ ላይ በብልፅግና ዕሳቤ ተገቢው ግንዛቤ ኖሯቸው ለውጡን በእውቀት መደገፍ የሚያስችላቸው አቅም የሚፈጥሩበት ስልጠና ስለመሆኑ በመድረኮቹ ተጠቁሟል።
ተቋምን ስንመራም ሆነ አገልግሎትን ስንሰጥ ሀገራዊ ተልእኮዎችን ተረድተን ቀጣይ ሀገራዊ አቅጣጫ ላይ በቂ ግንዛቤን በመጨበጥ ለሀገራዊ ብልፅግናችን እንድንተጋ የሚል መልእክት ተላልፏል።
ባለሙያው እና ነዋሪው የአመለካከትና የተግባር አንድነትን በመፍጠር የብልፅግና እሳቤን በተጨባጭ እንዲተገብር ስለሚያስችል ሰልጣኝ በቆይታቸው ሁሉ ስልጠናውን በከፍተኛ ዲሲፕሊን እንዲከታተሉ ጥሪ ተላልፏል።
መድረኩ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ዘርፍ እምርታ ላይ በቀረበ ሰነድ መድረኩ ተጀምሯል።


