ኢትዮጵያ በማንሰራራት ጉዞ ላይ ሆና የሚከበር በዓል

20ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ነገ ይከበራል

የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ነገ ህዳር 29/2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ በደማቅ ስነስርዓት ይከበራል።

በዓሉ ኅብረ ብሔራዊነታችንን ባጎላ መልኩ የሚከበር ይሆናል።

20ኛውን የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው “የኢትዮጵያውያን የምክክር ቀን” ሲምፖዚየም በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በዚሁ ወቅት እንዳሉት የብዝኃ ማንነት፣ ባህልና እሴት ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ሕዝቦች ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ሰርታለች፡፡

አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እንዳሉት ኅብረ ብሔራዊነታችንን ለብሔራዊ ጥቅማችን ማዋል አለብን።

ክልሎች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት መጎናፀፋቸውን በማንሳት የዘንድሮው በዓል አስተናጋጅ የሆነው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዚህ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በማንሰራራት ጉዞ ላይ ሆና የሚከበር በዓል መሆኑን ገልጸው፥ ኅብረ ብሔራዊነታችንን ለብሔራዊ ጥቅማችን ማዋል አለብን ነው ያሉት።

በዓሉ በአስተናጋጅ ክልሎች የልማት ስራዎች እንዲከናወኑና የኢኮኖሚ መነቃቃት እንዲፈጠር ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡

በዚህም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአጭር ጊዜ በሰባቱም ክላስተር ከተሞች የተከናወኑ የልማት እንቅስቃሴዎች ምስክር መሆናቸውን አመልክተዋል።

በሲምፖዚየሙ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገርን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *