“በመደመር መንግስት እይታ፤ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ በሁሉም የከተማ ወረዳ እና ገጠር ቀበሌ ሲሰጥ የነበረው ሶስተኛ ዙር ስልጠና ተጠናቋል።

በከተማ ወረዳና ገጠር ቀበሌዎች ላለፋት ሁለቱት ቀናት ቆይታ የነበረው ስልጠና “የመደመር መንግስት እይታ ፣ የግብርና እና የገጠር ልማት ትራንስፎርሜሽን እምርታ፣ የኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን እምርታ፣ የከተማ ልማት እና የቱሪዝም እምርታ” በሚሉ ርዕሶች ላይ ተሰቷል።

የስልጠናው ዋንኛ አላማም ማህበረሰቡ በመደመር መንግስት የሀገርን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በተለዩ ዋናዋና ዘርፎች የተቀመጡ የልማት ትልሞችንና የትግበራ አቅጣጫዎችን በመረዳት ለውጤታማነቱ ከመንግስት ጎን እንዲሰለፍ ግንዛቤ መፍጠር ነው ተብሏል።

በተሰጡ የስልጠና ርዕሶች ዙሪያ ሰልጣኞች በስፋት የተወያዩ ሲሆን በመድረኩም ለአስተዳደራችን ዘላቂ ሰላም እና ቀጣይነት ያለው የልማት ትልሞች ከመንግስታችን ጎን በመሰለፍ የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ የመድረኩ ተሳታፊዎች ሀሳብ የሰጡ ሲሆን መሰል መድረኮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ተወያዮች ጠይቀዋል።

በማጠቃለያው ከተሳታፊው ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችም ከመድረክ አወያይ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰቷል።

ማህበረሰቡ ያገኘውን እውቀት በመጠቀም ለሀገራዊ ብልፅግናችን ዘላቂነት የነቃ ተሳትፎን እንዲያደርግ ጥሪ ተላልፏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *