የለማች፣ የተከበረችና የታፈረች ኢትዮጵያን እናፅና – ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ

በፍትህና በዕኩልነት መሠረቶች ላይ የለማች፣ የተከበረችና የታፈረች ኢትዮጵያን እናፅና ሲሉ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ገለፁ፡፡

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ለብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በኤክስ ገጻቸው ባጋሩት መልእክት፤ “ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ ለ20ኛ ጊዜ ለሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን በፍትህና በዕኩልነት መሠረቶች ላይ በማዋቀር የለማች፣ የተከበረችና የታፈረች ኢትዮጵያን እናፅና ሲሉም ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *