በድሬዳዋ አስተዳደር በ9ጠኙ የከተማ ወረዳዎች እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን እርስ በእርስ በማስተሳሰር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ::

በድሬዳዋ አስተዳደር በዘጠኙ የከተማ ወረዳዎች እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ተገመገመ።

በዚህም በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በከተማ በወረዳዎች እየተከናወኑ የሚገኙት የኮሪደር ልማት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልፀው፤ በቅንጅት እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች በቀጣይም ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አመላክተዋል።

ከንቲባ ከድር አያይዘውም የድሬዳዋን የልማት ግስጋሴ በሚመጥን መልኩ የመንገድ ዳር ንግድ ቤቶችን እንዲሁም በአጠቃላይ አካባቢን ውብ፣ ፅዱ እና ለነዋሪዎች ምቹ አድርጎ ማልማት እንደሚገባ ገልፀዋል።

የኮሪደር ልማት ስራን እርስ በእርስ የማስተሳሰር ስራ መስራት እንደሚገባ ክቡር ከንቲባ ከድር አመላክተው፤ የተጀመሩ ስራዎችን በጥራት እና በፍጥነት በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ስራዎችን በፈጠራና በፍጥነት መስራት አስፈላጊ እንደሆነ እንዲሁም በኮሪደር ልማቱ በየአካባቢው የሚገኙ ቅርሶችን ቅርስነታቸውን በጠበቀ መልኩ የማልማት ስራ መሰራት እንደሚገባ የተናገሩት ደግሞ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ናቸው።

የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃለፊ አቶ ኢብራሂም ይሱፍ በበኩላቸው በወረዳዎች ያሉ ፀጋዎችን በመለየት ማልማት እንደሚገባ እንዲሁም ስራዎችን በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ማከናወን እንደሚገባ አመላክተው በኮሪደር ልማቱ በከተማ ማስዋብ ስራ ላይ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶችን ማሳተፍ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ከማህበረሰቡ ጋር ብሎም ከባለሀብቶች ጋር በመተባበር አካባቢን ውብ እና ሳቢ አድርጎ የማልማት ስራ ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጀ ፀጋዬ ተናግረዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *