የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ተኛ የስራ ዘመን 5ተኛ አመት 3ተኛ አስቸኳይ ጉባኤ አካሄዷል
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ተኛ የስራ ዘመን 5ተኛ አመት 3ተኛ አስቸኳይ ጉባኤ አጀንዳዎች አፅድቋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ተኛ የስራ ዘመን 4ተኛ አመት 10ተኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ አፅድቋል
እንዲሁም የተለያዩ ሹመቶችን ያፀደቀ ሲሆን በዚህ መሰረት:-
1,የአስተዳደሩ ምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲሀ አደን በገዛ ፍቃደቸ ስልጣን ለመልቀቅ የቀረቡት ጥያቄ ምክር ቤቱ ተወያይቶ አፅድቋል።በሳቸው ምትክም የተከበሩ አቶ አብዲ ሙክታር ሙሜ የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ -ጉባኤ ሆነው ተሹመዋል።
2 ወ/ሮ ሌሊሴ አህመድ ሀሰን የሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
3 አቶ ብሩክ ወርቅነህ የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
4 አቶ ፉአድ መሃመድ የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት ፅ/ቤት ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
በዳግማዊ ፍቃዱ


