በኮሪደር ልማቱ አካባቢያችንን ለማሳመር የጀመርነውን ስራ አጠናክረን እናስቀጥላለን ሲሉ በድሬዳዋ የወረዳ 4 እና 5 ነዋሪዎች ተናገሩ።
በድሬዳዋ አስተዳደር ዘጠኙንም የከተማ ወረዳዎች በኮሪደር ልማት አካባቢዎችን ውብ፣ ማራኪና ለነዋሪዎች ምቹ የማድረግ ስራ እየተከናወነ ሲገኝ፤ የወረዳ 4 እና 5 የኮሪደር የልማት ስራም የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን የማስዋብ፣ በመንገድ ከፈታ የተሽከርካሪና የእግረኛና መንገዶችን የማስፋት፣ የመንገድ ዳር መብራትና ሌሎችንም መሰረተ ልማቶችን ባካተተ መልኩ በጥራትና በፍጥነት እየተሰራ ይገኛል።
በዚህም የወረዳው ነዋሪዎች ልማቱ አካባቢያቸው ድረስ በመመጣቱ ደስተኛ መሆናቸዉን በመግለፅ፤ አካባቢያችንን በማልማቱ ረገድ ንቁ ተሳትፎ እያደረግን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ አያይዘውም የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን የትራንስፖርት ፍሰት ምቹ ለማድረግ፣ የኢንቨስትመንትና የንግድ እንቅስቃሴን ለማሳለጥ እንዲሁም ተወዳዳሪነቷን ከፍ ለማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ገፅታ ከመቀየሩ ባሻገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የጎላ መሆኑን ያመላከቱት ነዋሪዎቹ በቀጣይም ልማቱን አጠናክሮ በማስቀጠል ድሬዳዋን የማስዋብ ስራ በርብርብ እንደሚሰራ ገልፀዋል።


