የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ድሬዳዋን የቱሪዝም ማዕከል ማድረግ በሚቻልባቸው ነጥቦች ላይ በቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) ከተመራ ልኡካን ቡድን ጋር ተወያዩ
በዚህም ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ድሬዳዋን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ አስተዳደሩ ስራዎችን በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አመላክተዋል። አስተዳደሩ ከባለሀብቶች ጋር በጋራ በመሆንም ከተማዋ ያላትን የተፈጥሮ ፀጋዎች በመጠቀም የቱሪዝም መስህብ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ከንቲባ ከድር የገለፁ ሲሆን በአጠቃላይም ከተማዋን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን በመጥቀስ ሰፊ ማብራሪያ ሰተዋል። ድሬ ቀንም ለሊትም እንቅስቃሴ ያለባት ከተማ መሆኗን፣…


