የተፋሰስ ልማት ስራዎች በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረገገጥ ትልቅ አቅም እንዳላቸው ተገለፀ::
የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ለግብርና ሽግግር ስኬት 2018ዓ.ም እንደ ዋሂል ክላስተር በሀርላ ቀበሌ በተካሄደ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ተጀምሯል። በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የተፋሰስ ልማት የደን መራቆትን በመከላከል የደን ሽፋንን ለመጨመር፣የአፈርና ውሀ ጥበቃ ለማጎልበት፣የጎርፍ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ይረዳል።የከብት መኖ አቅርቦትን ለመጨመር ያግዛል ብለዋል። በዘንድሮው የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት የመሬት መራቆትን በ3.7…


