መረጃዎችን በማደራጀት፤ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የመምህራን መረጃ አስተዳደር ስርዓት (TMIS) ሶፍት ዌር በይፋ ተመረቀ::
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መረጃዎችን በማደራጀት፤ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እና ውሳኔዎችን በእውነት ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል ሶፍትዌር በዛሬው እለት አስመርቋል። በምረቃት መርሃ ግብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጅሀር ተገኝተው እንደገለፁት የትምህርት ካሪኩለም በማሻሻል የትምህርት ጥራትን በማሻሻል ረገድ አመርቂ ለውጦች እየተመዘገቡ መምጣታቸውን ገልጸዋል። ተቋሙ በትምህርት ዘርፍ የነበረውን አሰራር ወደ ዲጂታል የመቀየር ስራዎች በስፋት…


