መረጃዎችን በማደራጀት፤ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የመምህራን መረጃ አስተዳደር ስርዓት (TMIS) ሶፍት ዌር በይፋ ተመረቀ::

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መረጃዎችን በማደራጀት፤ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እና ውሳኔዎችን በእውነት ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል ሶፍትዌር በዛሬው እለት አስመርቋል።

በምረቃት መርሃ ግብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጅሀር ተገኝተው እንደገለፁት የትምህርት ካሪኩለም በማሻሻል የትምህርት ጥራትን በማሻሻል ረገድ አመርቂ ለውጦች እየተመዘገቡ መምጣታቸውን ገልጸዋል።

ተቋሙ በትምህርት ዘርፍ የነበረውን አሰራር ወደ ዲጂታል የመቀየር ስራዎች በስፋት እየተሰሩ መሆኑን እና ይህም ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ትልቅ አቅም መሆኑን ገልፀዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ በበኩላቸው የትምህርት ስራ መረጃን መሰረት ያደረገ የቴክኖሎጂዎችን አሰራሮችንን ማዘሙን አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ሆኗል፡፡ ቢሮው ይህንን የቴክኖሎጂ ሽግግር እውን ለማድረግ ባለፉት ጊዜያት ተጨባጭ ስራዎችን መስራቱን ተናግረዋል፡፡

በተቋሙ የበለጸገው ሶፍት ዌር ይህ ስርዓት መረጃዎቻችንን በማደራጀት፤ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት እና ውሳኔዎቻችን በእውነት ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑንም አስረድተዋል።

የቴክኖሎጂ ስርዓት “ፍጥነት እና ዘመናዊነትን’ ሲያላብሰን ይህ መጽሐፍ ደግሞ “ጥበብ እና ጥልቅ ልምድን’ ያወርስናል:: ሁለቱ ሲጣመሩ የድሬዳዋን ትምህርት ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግሩት እምነቴ ጽኑ ነው፡፡

እነዚህን ትልልቅ ስራዎች እውን ለማድረግም አስተዳደሩ ለትምህርቱ ሴክተር በሰጠው ልዩ ትኩረት መሆኑን የገለጽት ኃላፊው ለክቡር ከንቲባ እና ለካቢኔ አባላትም ምስጋና አቅርበዋል።

በመርሀ ግብሩም ከፈርጦች አንደበት የሚል በመምህራን ታሪክ ዙሪያ የተሰናዳ መጽሐፍት ተመርቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *