የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” በሚል በተሰናዳው እና ስድስት የሀገራችንን የፋይናንስ እና የገቢ ሥርዓት በመምራት ላይ ያሉ ዐበይት ተቋማት አፈፃፀም በሚገመግሙበት እና ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የሚኖራቸውን ስትራቴጂያዊ የቅድሚያ ምልከታ በሚያደርጉበት ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት በፋይናንስ አካታችነት ተጨባጭ እድገት ያስገኙ እና ሰፊ መዳረሻ ያላቸው የማክሮኢኮኖሚ ሪፎርሞች አካሂዳለች።

ከገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ሥርዓት እስከ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አፈፃፀሞች እና የዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ድረስ የእነዚህ አምስት ዓመታት ክንዋኔ በፋይናንስ ዘርፉ ተወዳዳሪነትን በሚያሳድጉ በመንግሥት ቆራጥ እና ስኬታማ ተግባራት የሚገለጥ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *