በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 03 እየተከናወነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ስራን አጠናክረን እናስቀጥላለን ሲሉ የወረዳው ነዋሪዎቹ ተናገሩ።
ከኮሪደር ልማቱ በፊት በአካባቢው ረጅም ጊዜ ሳይታደሱ የቆዩና ወጥ ያልሆኑ ቤቶች ይገኙ እንደነበረ ገልፀው አሁን ላይ በኮሪደር ልማቱ ያረጁ ቤቶች ዘመናዊና ውብ በሆነ መልኩ ተሻሽለው እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
ነዋሪዎቹ አያይዘውም ልማቱ ሲጠናቀቅ ለአካባቢው አዲስና ማራኪ ገፅታን እንደሚያላብሰው ጠቁመዋል።
በኮሪደር ልማቱ አካባቢው ላይ የሚገኙ ያረጁ ቤቶችን በአዲስ አሻሽሎ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የመገንባት እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የተዘጋጉ የእግረኛ መንገዶችን የመክፈትና አካባቢን ፅዱና አረንጓዴ የማድረግ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ እንደሚገኙ የተናገሩት ደግሞ የድሬዳዋ አሰተዳደር ፍትህ ፀጥታ ህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊና የወረዳው ደጋፊ አመራር አቶ አብዱሰላም አህመድ ናቸው።
የወረዳ 03 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ምትኩ ሁነኛው በበኩላቸው በኮሪደር ልማቱ አካባቢውን ፅዱ ከማድረግ በተጨማሪ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።


