የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የግብርና፣ ተፈጥሮ ሀብትና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመስክ ምልከታውን አጠናክሮ ቀጥሏል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የግብርና፣ ተፈጥሮ ሀብትና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው እለት በድሬዳዋ አስተዳደር የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስር ያሉ እህሎች፣ የቤት ቁሳቁስና የተለያዩ ለአደጋ ጊዜ ሚያስፈልጉ የእቃ ማስቀመጫ መጋዘኖችን ያሉበትን ሁኔታ ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡

በተከበሩ አህመድ አብዶ ሰብሳቢነት የሚመራው የግብርና፣ ተፈጥሮ ሀብትና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው እለትም የመስክ ምልከታውን አጠናክሮ ሲቀጥል ከተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች የተሰበሰቡ እህሎችን እንዲሁም በጎ ፍቃደኛ ከሆኑ ዲያስፖራዎችና የድሬዳዋ ወዳጆች ለአቅመ ደካማ ማህበረሰቦች የተሰበሰቡ እህልና ቁሳቁሶች በህጋዊ መንገድ ተደራሽ ይሆናሉ ወይ የሚለውን በመመልከት የእህሎቹን አያያዝና አቀማመጥንም ተመልክተዋል፡፡

ድንገተኛ አደጋዎች ሲፈጠሩ የመንግስት ሀላፊነት ነው ብሎ ከመቀመጥ ይልቅ ማህበረሰባችን እርስ በእርስ የመረዳዳት ባህሉን እንያጠናከረ ከውጪ እርዳታ ከመጠበቅ ይልቅ እርስ በእርስ እየተጋገዝንና እየተደጋገፍን ከተረጂነት የምንላቀቅበትን መንገድ በመፈለግ ሁሉም ዜጋ ለተቋሙ ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ ተጠቁሟ፡፡

በመጋዘን ውስጥ ለድንገተኛ አደጋ ተብለው የተቀመጡ በቆሎና ማሽላዎች በጥሩ ሁኔታ መቀመጣቸውን የተመለከተው ቋሚ ኮሚቴው መጋዘኖቹም ለድሬዳዋ አየር ፀባይ ተስማሚ መሆናቸውንም ተመልክቷል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በመጋዘን ውስጥ ያሉ ለቤት እቃ የሚውሉ ቁሳቁሶች የተቀመጡበጥ መንገድ መስተካከልና በካይዘን የታገዘ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ የጠቆሙ ሲሆን በቀጣይ በተቋሙ ላይ እቅድና ሪፖርቱን የመገምገም እንዲሁም ሰነዶቹን የመፈተሸ ስራ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሱሌይማን አሊ ከቋሚ ኮሚቴው የተነሱ ሀሳብና አስተያየቶችን በመውሰድ በተቋቸው ውስጥ የሰራተኛ እጥረት መኖሩን ለቋሚ ኮሚቴው አብራርተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *