የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በከተማ ሰራ አስኪያጅ እና ተጠሪ ተቋማቱ ላይ የመስክ ምልከታውን አደረገ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው እለት የከተማ ስራ አስኪያጅ ተጠሪ ተቋማት በሆኑ የፅዳትና ውበት ኤጀንሲ፣ የቄራ አገልግሎት ድርጅትንና መንገዶች ባለስልጣን ላይ የንብረት ማስቀመጫ መጋዘኖችን (እስቶሮች) ያሉበትን ሁኔታ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

በተከበሩ ወ/ሮ አንድነት ሀይሉ ሰብሳቢነት የሚመራው የመንግስት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በከተማ ስራ አስኪያጅ እና ተጠሪ ተቋማት በሆኑት የፅዳትና ውበት ኤጀንሲ፣ የቄራ አገልግሎት ድርጅትንና መንገዶች ባለስልጣን የንብረት ማስቀመጫ መጋዘኖች ለውጥ እያደረጉ መሆኑን የተመለከተ ሲሆን ከዚህ ቀደም የተሰጡ ግብረመልሶች ላይ አፈፃፀማቸውን በመመልከት የተሰሩ ስራዎች መኖራቸውን ተመልክተዋል፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ተጠሪ ተቋማት በኮሪደር ልማት ሰፊ ስራዎች እየሰሩ መሆኑን ያነሱት የተከበሩ ወ/ሮ አንድነት በመጋዘኖቹ ውስጥ መልሰው አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ንብረቶች እንዳሉ የተመለከቱ ሲሆን መጋዘን ውስጥ ለብዙ ጊዜያት እቃዎችን ከማስቀመጥ ይልቅ ወደ ስራ የሚገቡበትን መንገድ ማመቻቸት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ስራ በፈጠራ የታገዘ ስራ እንደመሆኑ መጠን በኮሪደር ልማት የተነሱ ብረቶች፣ ቆርቆሮዎች እና መሰል ንብረቶች ለአስተዳደሩ የልማት ስራዎች መልሰው ካልዋሉ ለብልሽ የሚዳረጉ በመሆኑ አሁን ላይ እየተሰራ ባለው ኮሪደር ልማት ላይ ታሳቢ ያደረገ ስራ መሰራት እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው ገምግሟል፡፡

የከተማ ስራ አስኪያጅና ተጠሪ ተቋማቱ ከፍተኛ ንብረት እንደሚያንቀሳቅሱት መጠን የተደራጀ መጋዘኖች (እስቶሮች) ሊኖራቸው እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው ያነሱ ሲሆን የንብረት ብክነትን ለመከላከል ካይዘንን ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር ስራዎች ተጠናክረው መሰራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

የከተማ ስራ አስኪያጅ ተጠሪ ተቋማት ስራዎችን ዲጂታላይዜሽን ከማድረግ አንፃር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የሚበረታቱ መሆኑን ያነሱት ቋሚ ኮሚቴው መጋዘኖች (እስቶሮች) ውስጥ ያሉ ንብረቶች በተደራጀ መልኩ ሼልፍ ላይ በአይነትና በቁጥር ለአሰራር ቀላል በሆነ መንገድ መቀመጥ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *