በአማረ ሃይማኖታዊ ስርዓት የተከበረው የጥምቀት በአል ያለ አንዳች የጸጥታ ችግር ፍጹም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እና ያለምንም የትራፊክ አደጋ ተከብሮ እንዲያልፍ በማድረግ ረገድ የድሬዳዋ ፖሊስ ሌሎች የፀጥታ አካላት እና አጋዥ የማህበረሰብ ክፍሎች ላደረጉት የላቀ አስተዋጾኦ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የድሬዳዋ ፖሊስ ከበአሉ አስቀድሞ እቅድ በማውጣትና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማወያየት ለበዓሉ ፍጹም ሰላማዊነት ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን የሚታወቅ ሲሆን ከከተራ አንስቶ እስከ እግዚአብሔር አብ ታቦት ድረስ ታቦታቱ ከወጡበት ደብር በአለ ጥምቀቱን በሀይማኖታዊ ስርአት አክብረው እስኪመለሱ ድረስ የድሬደዋ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት እና ሰላም ወዳድ የሆነው የከተማችን ነዋሪዎች ጋር ባከናወነው ቅንጅታዊ ስራ ውጤታማ መሆን መቻሉን የድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ገልጸዋል ።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም በማይዳሰሱ ቅርስነት ካስመዘገበቻቸው በዓላት መካከል አንዱ የሆነው ይህ የጥምቀት በአል ዘንድሮ በከተማችን ድሬዳዋ እንደ ከዚህ ቀደም ሁሉ የሌለው እምነት ተከታይ እህት ወንድሞች ለሀይማኖቱ ተከታይ የእንኳን አደረሳችሁ የፍቅር ስጦታ በማበረከት ከበዓሉ ፍጹም ሰላማዊነት ባሻገር መከባበር ፍቅርና አንድነትን በከተማችን ድሬዳዋ እንዲታይ ያደረገም ጭምር በመሆኑ የአስተዳደራችን ነዋሪዎች ላደረጉት ፍቅር ሁሉ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከልብ እንደሚያመሰግን ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ አስታውቀዋል።
ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ አክለውም ለተከታታይ ቀናት ከከተራ በአል አንስቶ እስከ እግዚአብሔር አብ ታቦት ወደ ደብሩ በሰላም እንዲገባ እና በአሉ በሰላም እንዲከበር በማድረግ ብሎም ለብአሉ ድምቀት የፈረሰኛ እጀባም ጭምር በመሰጠት በጀግንነት የመጠበቅ በሰብዓዊነት የማገልገል ተግባርን ላረጋገጡ የድሬዳዋ ፖሊስ አመራር እና አባለት እንድሁም ለሌሎች የፀጥታ አካላትም የላቀ ምስጋናቸውን ጨምረው አቅርበዋል ።
በአሉም ከከተራ አንስቶ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ያለ አንዳች የትራፊክ አደጋ እና የወንጀል ተግባር ፍጹም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ተከብሮ ማለፍ መቻሉም ታውቋል።


