የድሬዳዋ አስተዳደር የሰላም ም/ቤት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ እና የሰላም ኮንፍረንስ በዛሬው እለት አካሂዷል።
በጉባኤውም ተገኘተው መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በንግግራቸው
ከመደመር መንግስት ምስረታ ማግስት ጀምሮ ድሬደዋ ፍጹም ሰላም የሰፈነባት፣ለኑሮ ምቹ፤ለኢንቨስትመንት በእጅጉ ተመራጭ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በአስተዳደሩ በተፈጠረ ጠንካራ የአመራር ብቃት እና በፀጥታ አካላት ቅንጅት ስኬታማ ስራዎችን መስራት ተችሏል ብለዋል።
የተረጋገጠው ሰላም የማይመቻቸው እና እያስመዘገብነው ያለነው ስኬት እና ፈጣኑ የብልጽግና ጉዞአችን እንቅልፍ የሚነሳቸው አይኖሩም ማለት አይቻልም። በመሆኑም ሰላምን የማስጠበቅና ዘላቂ ሰላምና ደህንነት የማረጋገጡ ተግባር የሁሉንም ተሳትፎና ርብርብ የሚሻ ተግባር መሆኑንም ነዉ ክቡር ከንቲባው የገለጹት።
የድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህ ጸጥታ እና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላም መሀመድም የሰላም ምክር ቤቱ ከተቋቋመ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ አኩሪ ተግባሮች መስራቱን አንስተው በተለይም የአስተዳደሩን ሰላም በማጽናት በኩል ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ በርካታ ስራዎችን መስራታቸውን ተናግረዋል።
ቢሮውም በቀጣይ የሰላም ኮሚቴውን በመደገፍ ረገድ አስፈላጊውን የድጋፍና ክትትል ስራዉን እንደሚያጠናክርም ገልጸዋል።
በመድረኩም የ2018 ዓ.ም በጀት አመት የምክር ቤቱ የስድስት ወር ስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና የኢትዮጰያ የባህር በር ታሪካዊ ዳራ የሚዳስስ ጹሁፍ ቀርቦ በአባላቱ ውይይት ተደርጓል።
በመድረኩም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ክቡር አቶ አብዲ ሙክታር፣ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ ኡጋዞች፣ ሱልጣኖች የሰላም ምክር ቤት አደረጃጀቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የባህር በራችንን በሰላማዊ መንገድ እናስመልሳለን!


