የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽንና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከተማ ስራ አስኪያጅን የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዛሬው እለት የገመገመ ሲሆን በተካሄደው የመስክ ምልከታ የተሰሩ ስራዎችን መነሻ በማድረግ የከተማ ስራ አስኪያጅንና የተጠሪ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል፡፡
በዛሬው የውይይት ግምገማ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ የቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂምን ጨምሮ የተጠሪ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የቋሚ ኮሚቴው በተኙበት በእቅድ አፈፃፀሙ ላይ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ በጥንካሬና በውስንነት በተነሱ አፈፃፀሞች ላይ የጋራ መግባባት በመድረስ የመውጫ የግብረመልስ ውይይት አካሂዷል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽንና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ቤዛ ዳምጠው የከተማ ስራ አስኪያጅንና የተጠሪ ተቋማት የግብረመልሶች አፈፃፀም ተግባራዊ በማድረግ፣ በገቢ አፈጻጸሙ እየተደረገ ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ቤዛ ከተማ ስራስኪያጅና የተጠሪ ተቋማት ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጥ እያመጡ መሆኑን በመጥቀስ መንገዶች ባለስልጣን የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነትን በማስፋትና በመጠበቅ በከተማ እና በገጠር የመንገድ ግንባታና ጥገና ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አመርቂ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅና የተጠሪ ተቋማት ገቢን መሰብሰብና ማሳደግ በተመለከተ የተለያዩ የገቢ አማራጮችን በመጠቀም ተቋሙ ለህብረተሰቡ ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎችን በመስራት ምላሽ የሚሰጥበት መንገድ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧ፡፡
በመጨረሻም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽንና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከተማ ስራ አስኪያጅን የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ በቀጣይ ሊሻሻሉና ትኩረት ሊሰጡባቸው የሚገቡ ስራዎች መኖራቸውን በማንሳት የአዲሱ ቄራ በተመለከተ የውሃ ችግር በጊዜ ሊፈታ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡


