“ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ሰማይ ወሰን ሆኖ አያውቅም” – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ “ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ሰማይ ወሰን ሆኖ አያውቅም፤ የጀግንነት አሻራውን የሚያሳርፍበት፣ ብቃቱን የሚለካበት እና የሀገርን ኩራት የሚያውጅበት ሰፊ የመጫወቻ ሜዳው ነው” ሲሉ ገለጹ።

“ሰማዩ የኛ ነው” የሚል መርሁን በኩራት ለዘጠና ዓመታት አውጇል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ 90 ከቁጥር በላይ ነው የምንለው በምክንያት ነው ሲሉም አክለዋል።

“ዘጠኝ አሥርት ዓመታት የታተመ የማይበገር የአየር ክልልን የማስጠበቅ ፅናት፣ በሰማይ ላይ የተጻፈ የሉዓላዊነት ታሪክ፣ ዘመን የተሻገረ የነጻነት እና የአንድነት አርማ ነው” ሲሉ አየር ኃይሉን ገልጸውታል!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *