በወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት WRI(world resources institute) የCities for Africa ዳይሬክተር ዶ/ር አክሊሉ ፍቅረስላሴ የተመራ ልዑካን ቡድን በድሬዳዋ በሰንካሳ (SUNCASA) ፕሮጀክት የተሰሩ ስራዎችን ለመመልከትና ልምድ ልውውጥ ለማድረግ ድሬዳዋ ከተማ ገባ::
ከደቡብ አፍሪካ ጁሀንስፐርግ፣ ከሩዋንዳ ኪጋሊ እንዲሁም ከኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ፎር ሰስተነብል ዲቨሎፕመንት( international institute for Sustainable development) እና ወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት WRI ( world resources institute) የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና የመንግስት አካላት በድሬዳዋ በሰንካሳ ፕሮጀክት የተሰሩ ስራዎችን ለመመልከት ድሬዳዋ ከተማ ገብተዋል። ልዑኩ ድሬዳዋ ከተማ የገባው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት እንዲሁም በአስተዳደሩ በሰንካሳ ፕሮጀክት የተሰሩ ስራዎችን ለመመልከትና ተሞዕክሮ ለመለዋወጥ…


