ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የኢንስፔክሽንና የስነምግባር ኮሚሽን ሚና የላቀ መሆኑ ተገለፀ::

በድሬዳዋ አስተዳደር ሲካሄድ የቆነው የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የስነ-ምግባር ኮሚሽን እና የክልሎች፣ የከተማ አስተዳደር እና የፌደራል ተቋማት አደረጃጀት ኮምሽን የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ መንፈቅ ዓመት 9ኛው የጋራ የግምገማ መድረክ ተጠናቀቀ።

በዚህም በብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ደስታ ተስፋው (ዶ/ር) ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲና ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ የሚኖረው ፋይዳ ጉልህ መሆኑን ገልፀው፤ የፓርቲው ተልዕኮዎችን በሚገባ በመረዳት ጥራት ያለው አባላት በማፍራት አደረጃጀቶችን ማጠናከር ተግባራትን ፈትሾ መፈጸምና ውጤታማነትን ማረጋገጥ እንዲሁም የፓርቲ ጤንነት መጠበቅ ላይ በለፉት 6 ወራት አበረታች ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

በተጀመሩ የኢንስፔክሽን ሥራዎች የተገኘውን ምርጥ ተሞክሮ አጠናክሮ ማስቀጠል እና በክፍተት የታዩት ላይም በቀጣይ በርብርብና በትኩረት እንደሚሰራ ዋና ኮምሽነሩ ተናግረዋል።

የድሬዳዋ አሰተዳደር የኢንስፔክሽን እና የስነ ምግባር ኮሚሽን ኮሚቴ ሰብሳቢ ፋኪያ መሃመድ በበኩላቸው ከመድረኩ በርካታ ልምዶች የተቀሰሙበት መሆኑን ተናግረው፤ ኮሚሽኑ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ፣ፍትሀዊ እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን አስተዋፆ እንደሚወጣም ገልፀዋል።

ፓርቲው ጠንካራ እንዲሆን በማድረግ የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ የሚገኘው ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያመላከቱት ደግሞ በድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ጽ/ቤት ኃላፊ ኤልያስ አሊዪ ናቸው።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ኮሚሽኑ የፓርቲ እሴት የሚጨምሩ ተግባራት ላይ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው፤መድረኩ እርስ በእርስ ተሞክሮ በመቀያየር ለቀጣይ ስራ አቅም የሚፈጥሩ ልምዶችና አሰራሮችን የተገኘበት መሆኑን ጠቁመዋል።

በመጨረሻም ተሳታፊዎቹ ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት ኮምሽኑን ማጠናከር ወሳኝ በመሆኑ ቀጣይ ስራዎችን በርብርብና በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን አመላክተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *