የፌዴራል ተቋማት ብልፅግና ፓርቲ የኢኮኖሚ ክላስተር ወጣቶች ክንፍ በአስተዳደሩ በራስ አቅም የተሰሩ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
ከተጎበኙ የልማት ፕሮጀክቶች መካከልም ሲቪክ (ኮንቬክሽ) ሴንተር፣በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተጻፈው የመደመር ትውልድ መጽሐፍት ሽያጭ በተገኘው ገቢ እና በአስተዳደሩ ድጋፍ የተገነባውን እምርታ ቤተመጻሕፍትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በጎብኘቱም ወቅት የድሬዳዋ አስተዳደር ባህል እና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንደሰን አባይ በአስተዳደሩ አቅም የተሰሩ የልማት ስራዎችን ገለጻ አድርገዋል።
የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ዋና ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ገዛኸኝ አንዳርጌ በወቅቱ እንደገለጹት የለውጡ መንግስት መሰረተ ልማትን የማስፋፋት እና ትውልድን መገንባት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።
በአስተዳደሩ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ፈጠራ እና ፍጥነት ታክሎበት ጀምሮ በመጨረስ ለፍሬ እንዲበቁ የማድረግ ስራ መሰራቱን ያየንበት ነው ብለዋል።
በጎብኘቱ የተሳተፉ ወጣቶችም በአስተዳደሩ በራስ አቅም እና እውቀት እየተገነቡ የሚገኙት የልማት ፕሮጀክቶች ሀገሪቱ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ የሚያሳኩ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።


