ከደቡብ አፍሪካ ጁሀንስፐርግ፣ ከሩዋንዳ ኪጋሊ እንዲሁም ከኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ፎር ሰስተነብል ዲቨሎፕመንት( international institute for Sustainable development) እና ወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት WRI ( world resources institute) የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና የመንግስት አካላት በድሬዳዋ በሰንካሳ ፕሮጀክት የተሰሩ ስራዎችን ለመመልከት ድሬዳዋ ከተማ ገብተዋል።
ልዑኩ ድሬዳዋ ከተማ የገባው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት እንዲሁም በአስተዳደሩ በሰንካሳ ፕሮጀክት የተሰሩ ስራዎችን ለመመልከትና ተሞዕክሮ ለመለዋወጥ ሲሆን በቀጣይ በፕሮጀክቱ የሚሰሩ ስራዎች ላይም ምክክር የሚደረግ ይሆናል።
ልዑኩ ከጥር 18/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 21 በድሬዳዋ ቆይታ የሚያደርግ ሲሆን በነገው ዕለት ከአስተዳደሩ ጋር በፕሮጀክቱ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ምክክር ያደርጋል እንዲሁም በመስክ የተሰሩ ስራዎችን የሚጎበኝ ይሆናል ይሆናል።
ልኡክ ቡድኑ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።


