ለቀጣይ የሰንካሳ (SUNCASA) ፕሮጀክት ስኬታማነት እርስ በእርስ ተሞክሮዎችን መለዋወጥና ያጋጠሙ ችግሮች ላይ በጋራ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማመላከት አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ::

በካናዳ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ በሶስቱ ሰብሰሀራ አፍሪካ ከተሞች ማለትም በጁሀንስበርግ፣ በኪጋሊና በድሬዳዋ እየተተገበረ የሚገኘው የሰንካሳ (SUNCASA) ፕሮጀክት የስራ ሂደት ሪፖርት ቀርቦ ተገመገመ።

በዚህም በፕሮጀክቱ ትግበራ በድሬዳዋ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣውን ተፅእኖ መቋቋም የሚያስችሉና የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነትን የሚቀንሱ ስራዎች መሰራታቸውን በተጨማሪም የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች መሰጠቱ ተገልጿል።

በፕሮጀክቱ ከ7 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩ የተጠቆመ ሲሆን በአጠቃላይ በድሬዳዋ በሰንካሳ ፕሮጀክት አበረታች ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙና ለዚህም የማህበረሰቡና የአመራሩ ቁርጠኝነት የሚደነቅ መሆኑ ተገልጿል።

የዓለም አቀፍ የምርምር ተቋም ከሆነው (World Resources Institute) የአፍሪካ (Cities For Africa) ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አክሊሉ ፍቅረስላሴ በሶስቱ ከተሞች በፕሮጀክቱ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማና ማህበረሰቡን በስፋት ተጠቃሚ ያደረጉ መሆኑን ገልፀው፤ ከተሰሩ ስራዎች እርስ በእርስ በመማማርና ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቅሰም ለቀጣይ የፕሮጀክቱ ስራዎች ውጤታማነት ያጋጠሙ ችግሮች ላይ በጋራ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማመላከት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *