በወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት WRI(world resources institute) የCities for Africa ዳይሬክተር ዶ/ር አክሊሉ ፍቅረስላሴ የተመራ ከደቡብ አፍሪካ ጁሀንስፐርግ፣ ከሩዋንዳ ኪጋሊ እንዲሁም ከኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ፎር ሰስተነብል ዲቨሎፕመንት( international institute for Sustainable development) እና ከወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት WRI ( world resources institute) የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና የመንግስት አካላት ልኡካን ቡድን በትላንትናው እለት ድሬዳዋ ከተማ የገባ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ልኡክ ቡድኑ በሰንካሳ (SUNCASA) በፕሮጀክት የተሰሩ ስራዎች ላይ የልምድ ልውውጥ መድረክ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።


