በግማሽ ዓመት ውስጥ አጠቃላይ የስንዴ ምርት 126 ነጥብ 69 ሚሊየን ኩንታል ደርሷል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በ2018 የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሩብ ዓመታት አጠቃላይ የስንዴ ምርት 126 ነጥብ 69 ሚሊየን ኩንታል ደርሷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ይህም የመስኖ ስንዴ ምርትን ሳይጨምር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ የስንዴ ፕሮግራም ምርታማነትን በመጨመር፣ የመስኖ ሥርዓትን በማስፋት፣ የዘር አቅርቦት ሥርዓትን በማጠናከር ብሎም በዋና ዋና አካባቢዎች አነስተኛ አርሶ አደሮችን በመደገፍ…


