ወጣቶች በልማት እና በሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ በነቂስ መሳተፍ እንደሚገባቸው ተመላከተ።

የድሬዳዋ አስተዳደር የወረዳ 8 ወጣት ክንፍ ቅ/ጽ ቤት ከድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮምሽን ጋር በጋራ በመሆን የአስተዳደሩ አመራሮች ሰላምን በማስጠበቅና ልማትን በማፈጠኑ ረገድ ላበረከቱት አስተዋፆ የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር አካሂዷል።

እንዲሁም በመድረኩ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒነት እንዲኖረው የወጣቶች ሚና ላይ ስልጠና ተሰቷል።

በዚህም በመርሃ ግብሩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለገሀሬ በስፖርት፣ በጥበብ ስራዎች እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች ግንባር ቀደም መሆኗን ጠቅሰው የአሁኑ ትውልድም ይሄንን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባው እንዲሁም በአጠቃላይ

ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በተጀመረው ጉዞ ውስጥ ወጣቶች ግንባር ቀደም ሚና መወጣት እንደሚገባቸው ገፀዋል።

ከንቲባ ከድር አያይዘውም በቀጣይም ወጣቶች በልማት እና በሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ በነቂስ መሳተፍ እንደሚገባቸው አመላክተዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በበኩላቸው ወጣቶች ጊዜአቸውን በበጎ ተግባር ማሳለፋቸው የሚበረታታ መሆኑን ተናግረው በተለይም የወረዳ 8 ወጣቶች የወረዳውን ሰላም በማስጠበቅ እንዲሁም የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በማፋጠኑ ረገድ የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ወጣቶች ሁሌም እርስ በእርስ በመግባባት እና በአብሮነት ሰላምን ማስጠበቅ ይገባቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ደግሞ

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮምሽነር አለሙ መግራ ናቸው።

የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮምሽን ኮምሽነር ካሊድ መሀመድ የወረዳው ወጣቶች ከአመራሩ ጋር በመሆን በቅንጅትና በቅርበት የአካባቢን ሰላም በማስጠበቅ እንዲሁም ልማትን በማስቀጠልና በማፋጠን በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በመርሃ-ግብሩ ለክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ ለድሬዳዋ አስተዳደር ለብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እንዲሁም ለድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮምሽነር አለሙ መግራ የእውቅናና የምስጋና ሽልማት ተበርክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *