የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመጪው ማክሰኞ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግሥታቸውን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርቡ ምክር ቤቱ አስታውቋል።
በምክር ቤቱ 13ኛው መደበኛ ስብሰባ ላይ የሚቀርበው ይህ ሪፖርት፣ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ የታቀዱ ዋና ዋና የልማት እና የፖለቲካ ሥራዎች አፈጻጸምን የሚዳስስ ይሆናል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሡ ጥያቄዎችም ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።


