“የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ርዕይ እውን የሆነበት ወሳኝ ታሪካዊ ወቅት ላይ እንገኛለን” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

“የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት ርዕይ እውን የሆነበት ወሳኝ ታሪካዊ ወቅት ላይ እንገኛለን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ምረቃን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት፣ “የታዳሽ ኃይል አማራጮቻችንን በስፋት በማሳደግ፤ የሀገሪቱን እያንዳንዱን ማዕዘን እያበራን እንገኛለን” ብለዋል።

ይህ ጮራ የጎዳናዎችን ብርሃን ብቻ ሳይሆን የሕዝባችንን ተስፋ እና ነገም ጭምር ያበራ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ይህ ስኬት በቁርጠኝነት ከተነሣን እና አቅማችንን ካስተባበርን የራሳችንን የተፈጥሮ ጸጋ ተጠቅመን በኢነርጂ ረገድ ራስን የመቻል ግባችን ማረጋገጥ እንደምንችል ትልቅ ማሳያ እንደሆነ ነው የጠቆሙት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *