በድሬዳዋ አስተዳደር ከስደት ተመላሽ ወገኖችን በተለያዩ ሙያዎች አሰልጥኖ ወደ ስራ የማስገባት ተግባር በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለፀ::

መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ ኢሮፒያን ዩኒየን፣ ከእንግሊዝና ከስዊድን ኤንባሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ፅህፈት ቤት የተውጣጣ ልዑካን ቡድን ከስደት ተመላሾችን መልሶ የማቋቋም አቅምን የማሳደግ ስራዎች ላይ ከድሬዳዋ አስተዳደር ጋር ምክክር አድርጓል።

በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ስደተኛ እና ከስደት ተመላሽ ወገኞች የስራ እድል ከመፍጠር አኳያ እንዲሁም ስደትን በዘላቂነት ከመከላከል አኳያ በአስተዳደሩ አበረታች ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ በድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ኤጀንሲ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱረህማን ሙሳ ተናግረዋል።

ከተለያዩ ክልሎች በመምጣት በድሬዳዋ በኩል አድርገው ወደ ጎረቤት ሀገራት ለመሄድ ድንበር የሚያቋርጡ ዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ እንዲሁም ወንጀሉን ለመከላከል ይቻል ዘንድ የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት ( IOM ) ጋር በመተባበር የፍልሰተኞች ምላሽ መስጫ ( MRC ) ማእከል እያከናወነው የሚገኘው በሀገር አቀፍ ደረጃም በተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን የልኡክ ቡድኑ አባላት ገልፀዋል።

ልኡክ ቡድኑ በመስክ የፍልሰተኞች ምላሽ መስጫ ( MRC ) ማእከልን እንዲሁም የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን ተዘዋውሮ ጎብኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *