“ብሔራዊ ጥቅም የቡድን መጫወቻ ሊሆን አይገባም:- አምባሳደር ዲና ያነሱት ጥያቄ”

******************************

በዛሬው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሎ፣ የሀገርን ህልውና የሚፈታተን አንድ መራራ እውነት በጥያቄ መልክ ቀርቧል። በብዙ ሀገራት የፖለቲካ ልዩነት ቢኖርም፣ በ”ብሔራዊ ጥቅም” ላይ ግን የማይታለፍ ቀይ መስመር አለ። በኢትዮጵያ ግን…

ቁጭቱ፦ መንግሥታት ሲቀያየሩ የማይቀየር ቋሚ እሴት መሆን ሲገባው፣ ብሔራዊ ጥቅማችን ከሥልጣንና ከቡድን ጥቅም ጋር መተሳሰሩ ለሀገር ስጋት ሆኗል። አንዱ እንደ ድል የሚያየውን፣ ሌላው እንደ ስጋት የሚቆጥርበት አስከፊ መከፋፈል ውስጥ እንገኛለን።

አሳፋሪው እውነት፦ በሀገር ብሔራዊ ጥቅም ላይ የሚደራደሩ ቡድኖችንና ግለሰቦችን መመልከት ታሪክ ይቅር የማይለው አሳፋሪ ድርጊት ነው።

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው ወሳኝ ጥያቄ፦ “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ይህንን አደገኛ አካሄድ ከመሰረቱ ለመቀየር እና ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን ለይተን በአንድነት እንድንቆም ለማድረግ መንግሥት ምን እየሰራ ነው? የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል ለሚሉ የፖለቲካ ኃይሎችና ግለሰቦች ሁሉ የእርስዎ መልዕክት ምንድን ነው?”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *