የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቧቸው ጥያቄዎች

************

• በብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ የሚደራደሩ ዜጎች የሚታዩበት አሳፋሪ ሁኔታ ይስተዋላል፤ ይህን መሰረታዊ ሁኔታ ለመቀየር እና ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር ምን እየተሰራ ይገኛል?

• የወጣት ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ ምን ያክል ውጤታማ ሥራ እየተሠራ ነው? በዚህ ረገድ ለወጣቶች የተጀመሩ ብድሮች እና ወጣቶችን ወደ ሥራ የሚያሰማሩ ፕሮክቶችን በማካሄድ ረገድ ምን እየተሠራ ነው?

• መንግሥት አፈንግጠው ከሚወጡ ጋር ሲደራደር ብዙ ታጣቂ ካላቸው ጋር ለምን አይደራደርም?

• ልዩነቶቻችን አጥብበን በብሔራዊ ጥቅማችን ላይ በጋራ እንድንቆም መንግሥት ምን እየሠራ ነው?

• የኑሮው ውድነቱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን እየጎዳ ይገኛል፤ ይህን ችግር በቀጣይነት ለመፍታት ምን እየተሠራ ነው?

• በምናስመዘግበው ዕድገት ልክ የሆነ የሥራ ዕድል እና ምርታማነት እንዲፈጠር ምን እየተሰራ ነው?

• የጤና አገልግሎቱን ለማሻሻል የተጀመረውን ተስፋ ሰጪ ሥራ በመቀጠል ከመድኃኒት እና ሕክምና መገልገያዎች ጋር ተያይዘው የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ምን እየተሠራ ነው?

• የሕዝብ ሚዲያዎች ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚዲያ ሽፋን ለመስጠት ለምን አልቻሉም? መንግሥት ለተፎካካሪ ፓርቲዎች እኩል ሜዳ ለመፍጠር ምን እየሠራ ነው?

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ምላሽ እና ዝርዝር ማብራሪያ በኢቢሲ ዶትስትሪም የቀጥታ ስርጭት አሁኑኑ ይከታተሉ!

EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *